ወጋገን ባንክ ለኢትዮጵያ ልብ ህሙማን መርጃ ማዕከል 1 ሚሊየን ብር ድጋፍ ድጋፍ አደረገ

ጥቅምት 18/2014 (ዋልታ) ወጋገን ባንክ የ25ኛ ዓመት የብር እዮቤሊዩ የምስረታ በአል ምክንያት በማድረግ ለልብ ህሙማን መርጃ ማዕከል ድጋፍ አደረገ።
በልብ ህመም የሚሰቃዩ ኢትዮጵያውያንን መታደግ የሚቻለው በመተጋገዝና መተባበር መሆኑ ተገልጿል።
በአሁኑ ወቅትም ከ7 ሺሕ በላይ የልብ ህሙማን የህክምና ድጋፍ እንዲደረግላቸው እየተጠባበቁ ይገኛሉ፡፡
ባንኩ ማህበራዊ ሀላፉነቶቹን በመወጣት ላይ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን ለልብ ህሙማን መርጃ ማዕከል ያደረገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።
በሁሉም የአገሪቱ ክፍል 398 ቅርንጫፎች ያሉት ወጋገን ባንክ በሰሜኑ የአገሩቱ ክፍል በደረሰው የሰላም እጦትና አለመረጋጋት ከፍተኛ ተፅዕኖ እንደደረሰበት ገልጿል።
ሆኖም ያሉትን ፈተናዎች በመቋቋም የባንኩን 25ኛ ዓመት ምስረታ ምክንያት በማድረግ ለልብ ህሙማን መርጃ ማዕከል አሻራ ለማኖር መቻላቸውን የባንኩ ቦርድ ሰብሳቢ አብድሹ ሁሴን ገልጸዋል።
ከ25 ዓመታት በፊት በ16 ባለሀብቶች በብር 60 ሚሊዮን በተፈረመ መነሻ ካፒታል እና በብር 30 ሚሊዮን የተከፈተው የወጋገን ባንክ በአሁኑ ወቅት ካፒታሉን ወደ 3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ያደረሰ ሲሆን ጠቅላላ ካፒታል 5 ነጥብ 5 ቢሊዮን መድረሱ ተጠቅሷል።
በሃኒ አበበ