ዎርልድ ቪዥን ኢትዮጵያና የኦሮሚያ ክልል የ1∙7 ቢሊየን ብር የልማት ድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ

ዎርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ እና የኦሮሚያ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የአንድ ነጥብ 7  ቢሊየን ብር የ5 ዓመት የልማት ድጋፍ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ከድጋፉ ውስጥ 60 ከመቶ የሚሆነው ለህፃናት ዘርፍ ይመደባል ነው የተባለው።

ገንዘቡ ትምህርትን ለማስፋፋት፣ የውሃ አቅርቦትን ለማሻሻልና እና ለማህበረሰብ ልማት እንደሚውል ተገልጿል።

ስምምነቱን የዎርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ዳይሬክተር ካርመን ቲል እና የኦሮሚያ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ሃላፊ አቶ ቶሎሳ ደገፋ መፈራረማቸውን ኦቢኤን ዘግቧል።

ስምምነቱ በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ 21 ወረዳዎች ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገልጿል።