ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን የተቋቋመው የፖለቲካ ተልዕኮ ለማስፈጸም ነው -አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

መስከረም 1/2015 (ዋልታ) “በኢትዮጵያ የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶችን እንዲያጣራ በሚል የተቋቋመው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን የፖለቲካ ተልዕኮ ማስፈጸሚያ ነው” ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገለጹ።
ከምስረታው አንስቶ ኮሚሽኑ አወዛጋቢ እና ፖለቲካዊ አላማ ያለው እንዲሁም ከእናንተ በላይ እኔ አውቅላችኋላሁ የሚል አድሏዊ አቋም ያለው መሆኑን አምባሳደር ሬድዋን በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት የሰብአዊ መብት ጥሰት የፈጸሙ አካላትን ተጠያቂ ለማድረግ እየሰራ ባለበት ወቅት ኮሚሽኑ የኢትዮጵያን ስም የማጠልሸት ተግባር ላይ ቢጠመድም ከተቋቋመው አካል በትብብር ለመስራት የሚያስችሉ አማራጮችን ለመፈለግ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን አመልክተዋል።
ይሁንና ኮሚሽኑ ጭምብሉን በመግለጥ ኢትዮጵያ ላይ በኃይል ፍላጎቱን ሊጭን ተነስቷል ብለው ይህን ጣልቃ ገብነት በፍጹም አንቀበልም ብለዋል።