የሀይል እጥረት የእንግሊዝን ኢኮኖሚ እየፈተነው ይገኛል

ኅዳር 13/2015 (ዋልታ) እንግሊዝ ያጋጠማትን የሀይል እጥረት ተከትሎ ኢኮኖሚዋ በእጅጉ እየተፈተነ ይገኛል፡፡
እንደ የኢኮኖሚ ትብብር እና ልማት ድርጅት ትንበያ በፈረንጆቹ 2023 የእንግሊዝ ኢኮኖሚ በ0 ነጥብ 4 በመቶ ሲያሽቆለቁል በ2024 ደግሞ የ0 ነጥብ 2 በመቶ እድገት ያስመዘግባል፡፡ይህም እንግሊዝን የግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት ከሆኑት የቡድን ሰባት ሀገራት መካከል ዝቅተኛ የኢኮኖሚ እድገት ያስመዘገበች ሀገር ያደርጋታል ነው የተባለው፡፡
እንግሊዝ ከአውሮፓ ሕብረት አባልነቷ መውጣቷን ተከትሎ በከፍተኛ ሁኔታ ለአምራች ሰው ሀይል እጥረት መዳረጓ ለኢኮኖሚዋ ማሽቆልቆል በምክንያትነት ተጠቅሷል፡፡
በተጨማሪም የኮቪድ 19 ወረርሽኝ የሰዎችን የመስራት ፍላጎት ማቀዛቀዙም ይጠቀሳል፡፡
ይህን ተከትሎ ከፍተኛ ሀይል ለመጠቀም የተገደደችው እንግሊዝ በታሪኳ አይታው የማታውቀውን የሀይል ክፍያ ፈጽማለች፡፡
ሌላኛዋ የቡድን 7 አባል ሀገር ጀርመን በጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርቷ የ0 ነጥብ 3 በመቶ ማሽቆልቆል እንደሚያጋጥማት መረጃዎች እንደሚያመላክቱ ሞርኒንግ ስታር አስነብቧል፡፡

ካናዳ፣ ጃፓን፣ ጣሊያን፣ ጀርመን፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይና አሜሪካ የቡድን 7 አባል ሀገራት መካከል ናቸው፡፡