የሃይማኖት አባቶች በማኅበረሰብ ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

መጋቢት 4/2016 (አዲስ ዋልታ) የሃይማኖት አባቶች በማኅበረሰብ ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አባቶች እና ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ተጉዘው ከተገኙ አባቶች ጋር ውይይት አድርገዋል።

ተሳታፊዎች ሰላም እና ፀጥታን፣ የኅብረተሰቡን የልማት ፍላጎቶች፣ ቤተክርስቲያኒቷ ውስጥ ስላሉ የአስተዳደር ተግዳሮቶች ብሎም የሃይማኖት አባቶች በሀገራችን ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የሚኖራቸውን ሚና አስመልክተው የተለያዩ ሃሳቦችን አንስተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውይይቱን አስመልክተው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት “ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር የምናደርጋቸውን ውይይቶች በመቀጠል ዛሬ ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ተጉዘው በስብሰባው የተገኙትን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አባቶችን ተቀብለን ተወያይተናል” ብለዋል፡፡