የልዩ ዘመቻዎች ኃይል የአየር ወለድ ስልጠና ማጠናቀቂያ የአየር ወለድ ዝላይ ትርኢት በዱከም አካሄደ

የካቲት 24/2013 (ዋልታ) – የልዩ ዘመቻዎች ኃይል የአየር ወለድ ስልጠና ማጠናቀቂያ የአየር ወለድ ዝላይ ትርኢት በዱከም አካሄደ።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላን ጨምሮ ከፍተኛ የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች በተገኙበት በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የልዩ ዘመቻዎች ኃይል ማሰልጠኛ የአየር ወለድ ስልጠና ማጠናቀቂያ መርሐግብር በዱከም የአየር ወለድ ዝላይ ሜዳ ላይ አካሂዷል።

የዝላይ ትርኢቱ የልዩ ዘመቻዎች ኃይል አየር ወለድ የደረሰበትን ከፍተኛ አቅም የሚያሳይ መሆኑንና ሰልጣኞቹ ከአየር ወለድ ስልጠናው በተጨማሪ ልዩ ልዩ የኦፕሬሽናልና የውጊያ ስልጠናዎችን የወሰዱ መሆናቸው ተገልጿል።

በሌላ በኩል በልዩ ዘመቻዎች ኃይል ማሰልጠኛ ማዕከል ስር የሚገኘውን የአየር ወለድ ትምህርት ቤትን ለማጠናከር የአዲስ ህንጻ ግንባታ መሰረተ ድንጋይ ይቀመጣል ተብሏል።

በቢሾፍቱ የአየር ወለድ ትምህርት ቤት ግቢ አጠቃላይ የአየር ወለድ የስልጠና ሂደት ጉብኝትና የመሰረተ ድንጋይ ማስቀመጥ መርሐግብሩ እንደሚካሔድ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል።