የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌዴራል መንግስትን የ2014 በጀት አጸደቀ

ሰኔ 28/2013 (ዋልታ) – የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌዴራል መንግስትን የ2014 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ላይ ውይይት ካደረገ በኋላ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

ምክር ቤቱ ለበጀት አመቱ 561 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ረቂቅ በጀት ያፀደቀ ሲሆን፣ በጀቱ ምርታማነትን ለማሳደግ ትልቅ ትኩረት የሰጠ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የጸደቀው በጀት ከ2013 በጀት ጋር ሲነጻጸር የ18 በመቶ ብልጫ ያለው ሲሆን፣ የበጀቱን ስብጥር በተመለከተም ለመደበኛ የፌዴራል መንግስት ወጪዎች ብር 162 ቢሊየን እንዲሁም ለካፒታል ወጪዎች ብር 183.5 ቢሊዮን በጀት ተመድቧል፡፡

በተጨማሪም ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍ ብር 203.95 ቢሊዮን ሲሆን፣ ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ ብር 12 ቢሊዮን መመደቡ ነው የተገለጸው፡፡