የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ያቀረበው የቴሌቪዥን ጣቢያ ስያሜ ለውጥ ጥያቄ በባለስልጣኑ ተቀባይነት አገኘ

ሰኔ 28/2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ያቀረበለትን የቴሌቪዥን ጣቢያ ስያሜ ቅያሬ ጥያቄ ተቀበለ።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ ‘ትግራይ ቴሌቪዥን’ በሚል ስያሜ የሚታወቀው ጣቢያ ‘ይሓ ቲቪ’ የሚል ስያሜ እንዲሰጠው ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት እንዳገኘ ባለስልጣኑ ለኢዜአ ገልጿል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዳረጋገጠው የስያሜ ጥያቄው ምላሽ ማግኘቱን ተከትሎ ጣቢያው በቅርብ ቀናት ውስጥ የአየር ስርጭት ይጀምራል።