የመከላከያ ጦር ኮሌጅ እና ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ

ሰኔ 7/2013 (ዋልታ) – የኢፌዴሪ መከላከያ የጦር ኮሌጅ እና ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ኢትዮጵያ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡

ሰነዱን የመከላከያ ጦር ኮሌጅ አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ሀብታሙ ጥላሁን እና የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በኢትዮጵያ ዋና ተጠሪ ኒኮላስ ቮን አርክ መፈራረማቸውን ከኮሌጁ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ስምምነቱ የዓለም አቀፍ የሠብአዊ መብት ሕግና ተያያዥ የሠብአዊ መብት ድንጋጌዎች ኮሌጁ በሚሰጣቸው ስልጠናዎችና በሚያደርጋቸው ምርምሮች በተሻለ መንገድ እንዲካተቱና በኮሌጁ ሰልጣኞች ከፍ ያለ ግንዛቤ እንዲፈጥሩ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡