የሚኒስቴሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ከቶኒ ብሌይር ኢኒስቲትዩት የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ


መስከረም 30/2016 (አዲስ ዋልታ) የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ከቶኒ ብሌይር ኢንስቲትዩት የስራ ኃላፊዎች ጋር የተለያዩ ተግባራትን በትብብር ለመሥራት ተወያይተዋል።

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) በውይይቱ ላይ የቶኒ ብሊዬር ኢንስቲትዩት ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር ጋር የሚሰራቸው የትብብር ስራዎች ውጤት ያመጡና የእውነተኛ ትብብር ማሳያዎች ናቸው ብለዋል።

ይህንን ትብብር አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም ሚኒስትሯ ተናግረዋል።

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዲኤታው ነመራ ገበዬሁ (ዶ/ር) በበኩላቸው የቶኒ ብሊዬር ኢንስቲትዩት በተለይ በክትትልና ግምገማ ዘርፍ ለፕላንና ልማት ሚኒስቴር ስራ ጠንካራ የቴክኒክ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ከዚሁ ጋር የተያያዙ መመሪያዎችና ሌሎች አጋዥ ሰነዶች በጋራ እየተዘጋጁ መሆኑንም አብራርተዋል።

ከዚሁ ጋር የተያያዙ መመሪያዎችና ሌሎች አጋዥ ሰነዶች በጋራ እየተዘጋጁ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው አብራርተዋል።

የፐብሊክ ኢንቨስትመንት አስተዳደርን በተመለከተም በዩናይትድ ኪንግደም የዳበረ ልምድ መኖሩን በመግለጽ ኢንስቲትዩቱ ኩባንያዎችን የማስተሳሰርና ልምድ የሚገኝበትን መንገድ እንዲያመቻች ጠይቀዋል።

አንድ እቅድ አንድ ሪፖርትን በሁሉም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ለመተግበር እየተሰራ መሆኑም በውይይቱ ቀርቧል፡፡

ለ28ኛው የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብርት ለዉጥ ጉባኤ እየተደረገ ያለው ዝግጅትም በመድረኩ መቅረቡም ተጠቁሟል።

የቶኒ ብሊዬር ኢንስቲትዩት የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ማለዳ ብስራት ኢኒስቲትዩቱ ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር ጋር የጀመራቸውን የትብብር ስራዎች እንደሚያጠናክር ማረጋገጣቸውን ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።