የምርት ብክነትን መከላከል የሚያስችል የእህል ማከማቻ ቴክኖሎጂ ይፋ ሆነ

መጋቢት 15/2013 (ዋልታ) – በተባበሩት መንግስታት አለም አቅፍ የረሀብና የምግብ ዋስትና ፕሮግራም ማስተባበሪያ ያዘጋጀው “የእህል ምርት ከብክነት እንታደግ፣ ደህንነቱን እንጠብቅ” በሚል መሪ ሀሳብ አየር የማያስገባ የእህል ማከማቻ ቴክኖሎጂ ማሳያ ሀገር አቅፍ ወርክሾፕና አውደ ርዕይ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የምርት ብክነትን የሚያስቀር አየር የማያስገባ ቴክኖሎጂ ይፋ በተደርገበት ወቅት የሻያ ሾኔ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ያሬድ ሰርጸ በኢትዮጵያ ከሚመረተው አጠቃላይ ምርት በምርት ክምችት 12 ነጥብ 5 በመቶ፣ በድህረ ምርት ከ20 እስከ 30 በመቶ እንደሚባክን ገልጸዋል፡፡

እንደ ኢፕድ ዘገባ ቴክኖሎጂው ምርትን ከነቀዝ ከመከላከሉም ባሻገር አርሶ አደሮች ምርታቸውን ከነቀዝ ለመከላከል የሚጠቀሙት ኬሚካል በጤና ላይ የሚያስከትለውን ችግር የሚቀርፍ ነው ብለዋል፡፡

በወርክሾፑ የተለያዩ የግል ኩባንያዎች ምርትን ከብክነት የሚከላከሉ ቴክኖሎጂዎችን አቅርበዋል።

አየር የማያስገባ የእህል ማከማቻ ቴክኖሎጂ ማሳያ ሀገር አቀፍ ወርክሾፕና አውደ ርዕይ የግብርና ሚኒስቴር ተወካይ፣ የደረጃዎች ኤጀንሲ ተወካዮች፣ አለም አቀፍ ድርጅቶችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።