የሠራተኞችን ጥያቄ ደረጃ በደረጃ ለመመለስ መንግስት ጥረት እያደረገ መሆኑ ተገለጸ

ሚያዝያ 23/2015 (ዋልታ) የሠራተኞችን ጥያቄ ደረጃ በደረጃ ለመመለስ መንግስት ጥረት እያደረገ መሆኑን የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ ለሰራተኞች ጥያቄ እልባት ለመስጠት ከኢትዮጵያ የሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን አመልክቷል።

የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ዓለም አቀፍ የሠራተኞች ቀንን አስመልክቶ ባስተላለፈው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ኢትዮጵያን ለማልማት ያላሰለሰ ጥረት ለሚያደርጉ በሁሉም መስክ የተሰማሩ ታታሪ ሠራተኞችን የምናከብርበት እና የምናመሰግንበት ልዩ ቀን እንደሆነም አስታውቋል፡፡