የሥራ እድልና ክህሎት ማሳደግን አስመልክቶ ውይይት እየተካሄደ ነው

ጥር 3/2014 (ዋልታ) የሥራ እድልና ክህሎት ማሳደግን አስመልክቶ ከግል ተቋማት፣ ከንግዱ ማኅበረሰብ እንዲሁም ከሌሎች ባለድርሻ ተቋማት ጋር ውይይት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

አሸባሪው የሕወሓት ቡድን በከፈተው ጦርነት የግለሰብን ጨምሮ በርካታ ተቋማት ላይ ባደረሰው ውድመት ዜጎች ከስራ ዓለም እንዲወጡ ማድረጉን ተከትሎ ይህንን ለመቅረፍ አጋር ድርጅቶች እንዲሁም ባለድርሻ ተቋማት ለችግሩ እልባት ለመስጠት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል::

የወጣቶችን ትኩስ ኃይል ለአገር እድገት የሚኖረውን አስተዋጽዖ ለማሳደግ በስራ እድል ፈጠራ ያለውን ማነቆ መፍታት ሁነኛ መንገድ በመሆኑ የግሉም ይሁን የመንግሥት የልማት ድርጅቶች እንዲሁም የንግድ ዘርፍ ማኅበራት ያላቸው ሚና ላቅ ያለ ነው ተብሏል፡፡

ስለሆነም የስራ ክህሎትን በማሳደግ የስራ አጥነትን ተግዳሮት ታሪክ ማድረግ ያሻል ነው የተባለው::

በኢትዮጵያ 11 ከተሞች ላይ ለ70ሺሕ ወጣቶች የስራ ክህሎትን በማላበስ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠርም ለመስራት መታቀዱ ተመላክቷል፡፡

በሔብሮን ዋልታው

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://www.facebook.com/waltainfo
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!