የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ኬንያ ገቡ

ሰርጌ ላቭሮቭ

ግንቦት 21/2015 (ዋልታ) የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ቀድሞ ይፋ ባልተደረገ ጉብኝት ኬንያ መግባታቸው ተገለጸ።

የሞስኮ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የሚኒስትሩን ሰኞ ንጋት ላይ ናይሮቢ መግባት ይፋ ያደረገ ቢሆንም ለምን እንደመጡ ግን ዝርዝር ማብራሪያ አለመስጠቱን ቢቢሲ ዘግቧል።

በናይሮቢ የሩሲያ ኤምባሲ በትዊተር ገጹ “ፍሬያማ የሁለትዮሽ ግንኙነት ለሩሲያና ኬንያ” የሚል መልዕክት አስፍሯል።

ላቭሮቭ በያዝነው የፈረንጆች ዓመት ወደ አፍሪካ ሲመጡ ይህ የመጀመሪያቸው እንዳልሆነና በፈረንጆች ሐምሌ 2022 ግብጽ፣ ኮንጎ፣ ኢትዮጵያ እና ኡጋንዳን ጎብኝተው እንደነበርም ዘገባው አስታውሷል።