የሰላም ሚኒስቴር ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ጋር የተግባር እቅድ ላይ ውይይት አካሄደ

 

የሰላም ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ሰላማዊ የሆነ ሲቪል ሰራተኛ በመገንባ ህብረተሰቡን ማገልገል የሚችልና ዜጋውን የመገንባት አቅም ያለው የመንግስት ሰራተኛ ለመፍጠር ይቻል ዘንድ ከተቋሙ ጋር በጋራ መስራት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ብለዋል ፡፡

በልዩ ድጋፍና አርብቶ አደር አካባቢዎች የሰው ሀይል ማሟላትና ክትትል ማድረግ፣ የብሔራዊ በጎ ፍቃድ ማህበረሰብ አገልግሎት ተሳታፊዎች ድጋፍና ክትትል ማድረግ ፣ ለህዝብ አገልግሎት በሚሰጡ ተቋማት የሰላም ግንባታ ስራዎችን ማከናወን የሚሉ ጉዳዮች በሁለቱ ተቋማት የጋራ እቅድ ላይ ተካቷል፡፡

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር አቶ በዛብህ ገብረየስ እንደተናገሩት የተዘጋጀው የጋራ እቅደ በጋራ ለምናከናውናቸው ተግባራት የተሰጠንን ሀላፊነት ለመወጣት የሚያስችል እቅድ መሆኑን ገልፀው ኮሚሽኑ የሚጠበቅበትን ሀላፊነት ለመወጣት ዝግጁነትን ገልፀዋል፡(ምንጭ፡-የሰላም ሚኒስትር)