የሰላም የቤቶች ባንክ ምሥረታ ሥነሥርዓት ተካሄደ

ግንቦት 19/2013 (ዋልታ) – የሰላም የቤቶች ባንክ ምሥረታ ሥነሥርዓት ተካሄደ፡፡

ባንኩ በዓይነቱ ልዩና ትልቁ ሀገር አቀፍ ተቋም እንደሆነ በምሥረታ ማብሰሪያ መርኃግብር ላይ ተገልጿል።

ባንኩን በአምስት ወራት ጊዜ ለመመሥረት እንዲቻል የ2 ቢሊየን ብር የተፈቀደ ቢሆንም፣ በቀጣይ ሁለት ዓመታት ውስጥ ካፒታሉን ወደ 5 ቢሊየን ብር ለማሳደግ መታቀዱ ተጠቁሟል።

ሰላም የመኖሪያ ቤቶች ብድር ባንክ ለመኖሪያ ቤቶች የረዥም ዘመን ብድር ፍላጎትን የሚያሟላ 15% ዝቅ ባለ ቅድሚያ ክፍያ እና እስከ 30 ዓመት በሚደርስ ጊዜ የሚከፈል ብድር እንደሚሰጥ ተገልጿል።

የባንኩ መሥራች ኮሚቴ አባላት በሰጡት መግለጫ ባንኩ የ1 ሺህ ብር ዋጋ ያላቸውን 2 ሚሊየን ብዛት ያላቸውን የተፈቀዱ አክሲዮኖችን ለገበያ ማቅረቡን ገልጸው፣ አነስተኛ መግዛት የሚቻለው የአክሲዮን ብዛትም 10 መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የባንኩን አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ በክልል ከተሞች ቅርጫፎች እንደሚከፈትም ተጠቁሟል፡፡

ባንኩ ባለድርሻ የሆኑ ቤት አልሚዎችን ጨምሮ ከመንግስት እና ከግል አካላት ጋር እንዲሁም ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ጋር እንደሚሰራ አስታውቋል፡፡

(በአድማሱ አራጋው)