የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሁለት ዓለም አቀፍ የምርጫ ታዛቢ ቡድኖች እውቅና ሰጠ

የምርጫ ታዛቢ ቡድኖች

ግንቦት 19/2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለዓለም አቀፍ ሪፐብሊካን ኢንስቲትዩት (አይአርአይ) እና ለዓለም አቀፍ የዴሞክራቲክ ኢንስቲትዩት (ኤንዲአይ) የምርጫ ታዛቢ ቡድን የምርጫ መታዘብ እውቅና መስጠቱን አስታውቋል።

ቦርዱ የድርጅቶቹ የጋራ የታዛቢ ቡድን ያቀረበውን የጥናት ዘዴ በማየት እንዲሁም አለም አቀፍ ታዛቢዎች መሰረታዊ መርሆዎችንና የታዛቢዎች አለም አቀፍ የስነ-ምግባር ደንብ በተከተለ መልኩ እንደሚሰሩ ስምምነት ላይ በመድረስ የመታዘብ እውቅናውን እንደሰጠ ገልጿል።

በአለም አቀፉ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የተነሳ የታዛቢ ቡድኑ የሚያከናውነው የመታዘብ ተግባር የስፋት ውስንነት እንደሚኖረውና ይህንንም በሚያደርጋቸው ስራዎች እና ማጠቃለያዎች ላይ የሚገለጽ መሆኑን ታዛቢ ቡድኑ እና ቦርዱ በጋራ መግባባት ላይ መደረሱን ከቦርዱ የተገኘው መረጃ አመልክቷል።