ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ቅድሚያ ሰጥታ እየሠራች ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ

ኅዳር 29/2014 (ዋልታ) – ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ቅድሚያ ሰጥታ እየሠራች መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት ዛሬ ከጅቡቲ፣ ኬንያ፣ ዩጋንዳ፣ ሶማሊያ፣ ኤርትራ እና ከደቡብ ሱዳን መሪዎች ጋር ጥልቅ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
“ከሀገራቱ ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ መሥራታችንን እንቀጥላለን” ሲሉም አስታውቀዋል።