ሚያዚያ 01/ 2013 (ዋልታ) – የሶማሌ ክልል የስራ ኃላፊዎች በኬንያ በናይሮቢ ከሚገኙ የሶማሌ ክልል የዳያስፖራ አባላት ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እንዲጠናቀቅ ቦንድ በመግዛት፣ ገበታ ለሀገር እንዲሁም ኤምባሲውን የማስዋብ ስራን ለመደገፍ ቃል ገብተዋል።
በኬንያ የኢፌዲሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር መለስ ዓለም ሚሲዮኑ በኬንያ የሚገኙ የሶማሌ ክልል ባለሀብቶች ወደ ሀገራቸው ገብተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
የኢትዮጵያን ዕድገት እውን ለማድረግ ሁሉም ዜጋ አስተዋጽኦ እንደሚያስፈልግም አምባሳደር መለስ ገልፀዋል።
(ምንጭ፡- ኢፕድ)