የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ለሕጻናት ነፃ የዓይን ሕክምና አገልግሎት ሊሰጥ ነው

የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ቅዳሜና እሁድ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ለሕጻናት ነፃ የዓይን ሕክምና አገልግሎት እንደሚሰጥ አስታወቀ፡፡

ህክምናው የሚሰጠው በመድሃኒት፣ በመነጽር ህክምና ወይም በቀዶ ጥገና መፍትሄ ማግኘት ላልቻሉ ሕጻናት ብቻ መሆኑንም ገልጿል፡፡

ህክምናው ዓይነ ስውርነትንና የዕይታ ችግሮችን ለመከላከል የተዘጋጀ ልዩ የነጻ ምርመራ ፕሮግራም ነው።

ወላጆችና አሳዳጊዎች ከ3 ወር እስከ 15 ዓመት የዕድሜ ክልል ያሉ ምንም ዓይነት የዓይን ምርመራ አድርገው የማያውቁ ወይም ችግር ኖሮባቸው ህክምና ያላገኙ ልጆቻቸውን ይዘው እንዲመጡ ጥሪ አቅርቧል፡፡

የህክምና ምርመራው ለሁለት ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 2 : 30 እስከ 8 : 30 እንደሚሰጥ ነው የተጠቀሰው፡፡

ምርመራው የዕይታ ችግርን፡ ዓይነ ስውርነትን እንዲሁም የልጆችን ዕይታ ለማስተካከል ያለመ ነው ተብሏል።

ይህ ፕሮግራም ከዚህ በፊት ህክምና ሲያገኙ የነበሩና ክትትል እየተደረገላቸው የሚገኙ ልጆችን እንደማያካትት ከቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡