የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ድጋፍ ለመከላከያ ሰራዊት  

መስከረም 14/2014 (ዋልታ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለአገር መከላከያ ሰራዊት 284 የእርድ እንስሳት እና 40 ኩንታል ስንቅ ድጋፍ አደረገ።

በክልሉ ከተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች ህብረተሰቡ ያዋጣውን ድጋፍ የአገር ሽማግሌዎችና የማህበረሰብ ተወካዮች ለአገር መከላከያ ሰራዊት አስረክበዋል።

ክልሉ ከዚህ ቀደም 20 ሚሊየን ብር ግምት ያለውን ተመሳሳይ ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል።

በተያያዘም በአሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተስፋ ለኢትዮጵያ በተባለ ድርጅት አማካኝነት 52 ሺሕ የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ አድርገዋል።

ኢዜአ እንደዘገበው በኒውዮርክ፣ ኒውጀርሲ እና ሌሎችም አካባቢዎች የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ናቸው የገንዘብ ድጋፉን ያደረጉት።