የብልጽግና ፓርቲ የማኒፌስቶና የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 08/2013 (ዋልታ) – የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዝዳንት ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ፓርቲው በምርጫ ወቅት የሚጠቀምበትን ማኒፌስቶና የምርጫ መወዳደሪያ ምልክትን ይፋ አድርገዋል፡፡

“ሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት ለጋራ ብልጽግና” በሚል መሪ ሃሳብ የብልጽግና ፓርቲ ማኒፌስቶ እና የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት ይፋዊ የእውቅና መድረክ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ይፋ ባደረጉት የመወዳደሪያ ምልክት የብልጽግና ፓርቲ ይፋዊ የመወዳደሪያ ምልክት እየበራ ያለ አምፖል መሆኑ ታውቋል፡፡

በመርሐግበሩ የፓርቲው ፕሬዚዳንት ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ በርካታ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡