የቦሌ አየር ማረፊያ የአየር ትራፊክ መቆጣጠሪያ ማማ የማስፋፊያ ፕሮጀክት ተመረቀ

ግንቦት 12/2013(ዋልታ) – የቦሌ አየር ማረፊያ የአየር ትራፊክ መቆጣጠሪያ ማማ የማስፋፊያ ፕሮጀክት በዛሬው እለት ተመርቋል፡፡

ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር በፊት ግንባታው በቻይናው ሲሲሲ ኩባንያ ተጀምሮ ለምረቃ የበቃው የአየር ትራንስፖርት መቆጣጠሪያ ማማው 48 ሚሊየን ብር ገደማ ወጪ ተደርጎበታል ተብሏል።

በምረቃ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የትራንስፖርት ሚኒስትር ዳግማዊ ሞገስን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

(በሱራፌል መንግስቴ)