የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ምክትል ፀሃፊ በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጉብኝት ጀመሩ

ሐምሌ 22/2013 (ዋልታ) – የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ምክትል ጸሃፊና የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፍትስ በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን የስድስት ቀናት ጉብኝት ጀምረዋል፡፡
በጉብኝቱ ወቅት ግሪፍትስ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን እና ከሰብአዊ እና ለጋሽ ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር ተገናኝተው ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል ፡፡
በቅርቡ የተሾሙት አስተባባሪው በስራቸው የመጀመሪያውን ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ በማድረጋቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡
ማርቲን ግሪፍትስ በቆይታቸው በትግራይ እና አማራ ክልሎች ጉብኝት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅሀፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡