የአሸባሪው ቡድን በምስራቅ ግንባር የነበረው እቅድ በመከላከያ እና በአፋር ልዩ ሃይል ከሸፈ

አሸባሪው የህወሃት ቡድን በምስራቅ ግንባር የነበረው እቅድ በሀገር መከላከያ ሰራዊት እና በአፋር ልዩ ሃይል የጋራ ቅንጅት መክሸፉን ምንጮች ለኢዜአ ገለጹ።

ሐምሌ 22/2013(ዋልታ) – አሸባሪው የህወሃት ቡድን በምስራቅ ግንባር የነበረው እቅድ በሀገር መከላከያ ሰራዊት እና በአፋር ልዩ ሃይል የጋራ ቅንጅት መክሸፉን ምንጮች ለኢዜአ ገለጹ።

ሽብርተኛው የህዋሃት ቡድን ለትግራይ ክልል ህዝብ ጥቅም ሲባል የቀረበውን የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔን ወደጎን በማለት በእኩይ ሀገርን የማፍረስ ሴራው ገፍቶበታል።

ቡድኑ ወክዬዋለው ለሚለው የትግራይ ህዝብ እንኳን ግድ የሌለው መሆኑን በተግባር እያሳየ ይገኛል።
ከሰሞኑ ለሰብዓዊ እርዳታ የሚውሉ የአስቸኳይ ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ የድጋፍ ቁሳቁሶችን የጫኑ ከ170 በላይ ተሽከርካሪዎች ጉዞ እንዲደናቀፍ አድርጓል።

ቡድኑ የሀገርን አንድነት ለማናጋት ውሸትን በሚያሰራጩለት የውጭ ሀገራት ቅጥረኛ ቡድኖች ጋር በመሆን ኢትዮጵያ እንዳትረጋጋ እንዲሁም በዜጎች መካከል ጥርጣሬ እንዲነግስ ሌትተቀን በመስራት ላይ ነው።

አሸባሪው የህወሃት የጥፋት ቡድን ከዚህ ቀደም በሀገር መከላከያ ሀይል ላይ የፈጸመው ክህደት ሳያንሰው አሁንም በአፋር እና በአማራ ክልሎች ላይ ትንኮሳ በማድረግ ምንም የማያውቁ ህጻናት ልጆችን የእሳት እራት በማድረግ ላይ ነው።

የጁንታው ጥቃት በተከለፈተባቸው ሁለቱ ክልሎችም እራስን ለመከላከል በሚደረጉ ጥረቶች ለውትድርና ያልደረሱ ልጆች ዋጋ እየከፈሉ መሆኑን የተማረኩት ህጻናት በአንደበታቸው ሲናገሩ እንደነበር ይታወሳል።

ሽብርተኛው ከሰሞኑ በአፋር ክልል ዞን አራት እዋ በተባለው ወረዳ ተኩስ ሲከፍት በተወሰደበት የማያዳግም እርምጃ የሽብርተኛው ህዋሃት አክርካሪው መመታቱም ተጠቅሷልዕ።

በውጊያው ቡድኑ ያሰለፋቸው በርካታ ታጣቂዎች መሞታቸው እና መማረካቸውንም ምንጮች ለኢዜአ አስረድተዋል።
በተወሰደው እርምጃም የሽብር ቡድኑን ከአካባቢው ጠራርጎ ለማስወጣት የአፋር ልዩ ሀይልና መከላከያ በቅንጅት በወሰዱት እርምጃ የተማረኩ የጁንታዉ አመራሮች በሰጡት ቃል እምቢተኛው የሽብር ቡድን ህዋሃት በአፋር ክልል በድምሩ ሶስት ክፍለ ጦሮችን አሰማርቶ እንደነበር አስረድተዋል።

አንደኛው ክፍለ ጦር በተወሰደበት ከባድ እርምጃ ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ መሆኑና መደምሰሱን አረጋግጠዋል።
የአሸባሪው ቡድን የተቀሩት ሁለቱ ክፍለ ጦሮች ደግሞ ከፍተኛ የሆነ የቀለብ፣የጥይትና መሰል የሎጀስቲክስ አቅርቦት ችግር ውስጥ እንዳሉ ምርኮኛ አመራሮች በማማረርና በስሜት ማስረዳታቸውን ምንጮቻችን ለኢዜአ አረጋግጠዋል፡፡

የሀይል መዳከም የታየበት አሸባሪ ቡድኑ በአፋር ልዩ ሃይልና በመከላከያ ሰራዊት ተመቶ እንዲመለስ መደረጉም ታውቋል።
በዚህ ግንባር አሸባሪው የህወሃት ቡድን በደረሰበት ጉዳት ምክንያት በምስራቅ ግንባር የነበረው እቅዱ መክሸፉ ተገልጿል።

በሌላ በኩል ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ መንግስት የተናጠል ተኩስ አቁሞ አከባቢውን ለቆ በወጣበት ሁኔታ ሽብርተኛው ህወሓት ህፃናትን ሲያስጨፈጭፍ በዝምታ ማየቱን ቀጥሎበታል።

ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ የትግራይ ህዝብ የእርዳታ እህል እንዳይደርሰው ሽብርተኛውን ቡድን እንደመውቀስ መንግስት ላይ ጫና ለማሳደር የሚያደርገው እንቅስቃሴ ብዙዎችን ያስገረመ ጉዳይ ሆኗል።