የተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ ልዑክ ጅግጅጋ ገባ

መጋቢት 12/2014 (ዋልታ) የተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ ልዑክ ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ገባ፡፡

ለልዑኩ የሶማሌ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አብዲራህማን አሕመድ ሀሰንና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በገራድ ዊልዋል አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል አድርገዋል።

በኢትዮጵያ የመንግሥታቱ የሰብኣዊ ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር ካትሪን ሶዚ (ዶ/ር) ከመንግሥታቱ የልማት ፕሮግራም (ዩኤንዲፒ) የኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር ቱርሃን ሳሌህ ጋር በመሆን ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሀመድ ዑመር ጋር ይገናኛሉ ተብሏል፡፡

የጉብኝታቸው ዓላማም በድርቅ ሁኔታና በማኅበረሰቡ ልማት ዙሪያ ያሉ ችግሮችን ለመወያየትና ለመፍታት እንደሆነ ከክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW