ሳማንታ ፓወር በተያዘው ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ፣ ኬኒያ እና ሶማሊያ እንደሚያቀኑ ገለጹ

ሐምሌ 12/2014 (ዋልታ) የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስ ኤአይዲ) ኃላፊ ሳማንታ ፓወር በተያዘው ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ፣ ኬኒያ እና ሶማሊያ እንደሚያቀኑ ገልጸዋል፡፡

ኃላፊዋ በአገራቱ በሚኖራት ጉብኝት ድርቅን ተከትሎ እየተከሰተ ባለው ሰብአዊ ቀውስ ምክንያታ የተጎዱ ዜጎችን እንደሚጎበኙ አስታወቀዋል፡፡

ሳማንታ ይህንን ያሉት የሚያስተዳድሩት ተራድኦ ድርጅት ለአፍሪካ ቀንድ አገራት 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር ገደማ ድጋድ ማድረጉን ይፋ ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡

ድጋፉ በኢትዮጵያ በኬኒያ እና በሶማሊያ ለሚገኙ ዜጎች አስቸኮይ እርዳታ የሚውል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ድጋፉ ለአደጋ ጊዜ የሚሆኑ ምግቦች፣ ቀጥተኛ የገንዘብ ድጋፍ ፣ ክትባት ፣ ለተላላፊ በሽታዎች ህክምና እና ለአደጋ ተጋላጭ ለሆኑ ሴቶች እና ህጻናት ለሚውሉ አገልግሎቶች እንደሚውል አስረድተዋል፡፡