የትራምፕ “ድምጽ አጭበርብሩልኝ” የስልክ ንግግር ይፋ ሆነ

ትራምፕ ስልክ እየደወሉ ጆ ባይደንን እንዳሸንፈው ትንሽ ድምጽ እንዴትም ብላችሁ አሟሉልልኝ እያሉ የግዛት አስመራጮችን ይለምኑ እንደነበር ዋሺንግተን ፖስት አጋለጠ።

ተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ባለፈው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ጆ ባይደንን እንዳሸንፍ ድምጽ ከየትም ብላችሁ ፈልጉ እያሉ ከደወሉባቸው የግዛት የምርጫ ኃላፊዎች አንዱ የጆርጂያ ግዛት ምርጫ አስፈጻሚ ብራድ ራፍነስፐርግ ናቸው።

ዋሺንግተን ፖስት ይፋ ባደረገው የስልክ ቅጂ ንግግር ትራምፕ 11ሺ 780 ድምጽ ከየትም ብለህ ፈልግ እያሉ ሲለምኑ እንደነበር ያሰማል።

ብራድ በበኩላቸው የጆርጂያ ግዛት ቆጠራው በትክክል ተቆጥሮ መጠናቀቁን ለትራምፕ ሲናገሩ ይሰማሉ።

ሆኖም ትራምፕ አስፈጻሚውን በማባበልና በማግባባት ትንሽ የተጭበረበሩ ድምጾችን ካገኘ እሳቸው አሸናፊ እንደሚሆኑ በማስረዳት እንደምንም ተባባሪ እንዲሆን ሲያበረታቱት ተሰምቷል።