የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫ ኤጀንሲ የቀጣይ 10 አመታት መሪ ዕቅድ ለባለድርሻ አካላት ይፋ አደረገ

   የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫ ኤጀንሲ

የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫ ኤጀንሲ የቀጣይ 10 አመታት መሪ እቅድ ሰነድ ለባለ ድርሻ አካላት ይፋ አደረገ።

ኤጀንሲው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ ከክልል አቃቤ ህግና ባለድርሻ አካላት ጋር በእቅዱ ዙሪያ ውይይት አድርጓል።

የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ሙሉቀን አማረ ጥራቱን የጠበቀ የሰነድ አገልግሎት ለመስጠትና በኢንፎርሜሽን የታገዘ አገልግሎት ለማድረስ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ በተቋማት መካከል ቅንጅታዊ አሰራር አለመኖር፣ የኑሮ ውድነትና ብልሹ አሰራሮች በኤጀንሲው አሰራሩን ለማዘመን ፈታኝ ሁኔታዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

ከ2003 እስከ 2012 ዓ.ም በነበሩት ሁለት መሪ እቅዶች ተሞክሮ በመውሰድ ለቀጣይ 10 ዓመታት የዕቅድ መስኮች የላቀ ሰነድ ማረጋገጥ ህጋዊ ደህንነቱ የተጠበቀ የቋትና አስተዳደር መዘርጋት የተቋማት አገልግሎት ግንባታ የትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸውን አስታውቀዋል።

በሀሰተኛ ሰነዶች ምክንይት የሚፈጠሩ ወንጀሎችን መከላከል፣ ግልጽነት እና ተጠያቂነት የሰፈነበት የአሰራር ስርዓት መዘርጋት እንደሚገባም ተገልጿል።

(በሀኒ አበበ)