የትራንስፖርትና ሎጅስቲክ ዘርፍ ለዕድገትና ልማትን ለማቀላጠፍ አይነተኛ ሚና አላቸው- ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

መጋቢት 15/2013 (ዋልታ) – በአይነቱ የመጀመሪያ በሆነው የትራንስፖርት ዘርፍ የኢንቨስትመንት ጉባኤ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክ ዘርፍ ለዕድገትም ሆነ ልማትን ለማቀላጠፍ አይነተኛ ሚና አላቸው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የመጀመሪያ በሆነው የትራንስፖርት ዘርፍ የኢንቨስትመንት ጉባኤ ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል መካሄድ ጀምሯል።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በዘርፉ የቢዝነስ አማራጭ ለመሠማራት የሀገር ውስጥና አለም አቀፍ ባለሀብቶች በጉባኤው በመገኘታቸው አመስግነዋል፡፡

የትራንስፖርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ በበኩላቸው፣ የትራንስፖርት ዘርፍ የኢንቨስትመንት ጉባኤ ለግሉ ዘርፍ አሳታፊ የሚያደርግ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በጉባኤው ሶስት የሎጅስቲክስና የወደብ አገልግሎት ሰጪ ኩባንያዎች እንዲሁም 300 የሚደርሱ የዘርፉ ተቋማት ተሳታፊ ሆነዋል።

(በሰለሞን በየነ)