የቻይናው ፕሬዝዳንት ሞስኮ ገቡ

መጋቢት 11/2015 (ዋልታ) የቻይና ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ሞስኮ ገብተዋል፡፡

የፕሬዝዳንቱ የሞስኮ ጉብኝት የዩክሬይን-ሩሲያ ጦርንት ከተጀመረ ወዲህ የመጀመሪያቸው መሆኑ ተነግሯል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ሞስኮ ሲገቡ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ “ጉብኝቱ ፍሬያማ እንደሚሆን እና ለቻይና-ሩሲያ ግንኙነት ጤናማ እና የተረጋጋ እድገት አዲስ ኃይል እንደሚሰጥ እርግጠኛ ነኝ” ብለዋል፡፡

የዢ ጂንፒንግ ጉብኝት የሩስያ እና ዩክሬይንን ጦርነት በማስቆም ዙሪያ እንደሚመክሩ የተገለጸ ሲሆን ፕሬዝዳንቱ በዚህ ዙሪያ በሰጡት አስተያዬት “የዩክሬን ቀውስን ለማስቆም እኛ ያቀረብነው ሀሳብ ዓለም አቀፋዊ አመለካከቶችን የሚያንፀባርቅ ነው” ማለታቸውን አልጃዚራ ዘግቧል።

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በበኩላቸው የመልካም ወዳጄ ጉብኝት ትልቅ ተስፋ አለው ሲሉ ገልጸው ቻይና ጥሩ ጎረቤት እና አስተማማኝ አጋር ናት በማለትም አሞካሽተዋል፡፡