የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ማስተካከያ ተደረገ

ነሐሴ 23/2015 (አዲስ ዋልታ) ከዛሬ ነሐሴ 23/2015 ጀምሮ ለአንድ ወር የሚቆይ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ይፋ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ የዓለም ነዳጅ ዋጋ ከሚያዝያ ወር 2015 ጀምሮ እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ ድረስ አንጻራዊ መረጋጋት እንደታየበት ገልጿል።

በዚህም ላለፉት አራት ወራት በችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ለውጥ ሳይደረግ መቆየቱን አስታውሷል።

ሆኖም ግን የዓለም ነዳጅ ዋጋ ከሐምሌ ጀምሮ የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ እያሳየ በመምጣቱ ዋጋውን ማሻሻያ ማድረግ ማስፈለጉ ተገልጿል፡፡

በዚሁ መሰረት

1. ቤንዚን ———-ብር 74.85 በሊትር
2. ነጭ ናፍጣ ———–ብር 76.34 በሊትር
3. ኬሮሲን ብር ————76.34 በሊትር
4. የአውሮፕላን ነዳጅ ———ብር 68.58 በሊትር
5. ቀላል ጥቁር ናፍጣ ———–62.22 በሊትር
6. ከባድ ጥቁር ናፍጣ ———–61.07 በሊትር መሆኑም ተመላክቷል፡፡