የኒያ ፋውንዴሽን እና የጆይ ኦውቲዝም ማዕከል መሥራች ወ/ሮ ዘሚ የኑስ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

ግንቦት 03 /2013 (ዋልታ) የኒያ ፋውንዴሽን እና የጆይ ኦውቲዝም ማዕከል መሥራች ወይዘሮ ዘሚ የኑስ በኮሮና ቫይረስ ፅኑ ህክምና ማዕከል ውስጥ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ህይወታቸው ማለፉ ተነገረ።
ዘሚ የኑስ በአሁኑ ሰአት ከ200 በላይ ለሚሆኑ የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸውን ልጆች እንክብካቤ እያደረጉ እንደሚገኙ ከቅርብ ቤተሰቦቻቸው ያገኘውን መረጃ ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል።