የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድርና የአሜሪካ አምባሳደር ተወያዩ

ጥቅምት 12/2014 (ዋልታ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ጊታ ፓሲ ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱ ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) አሸባሪው የትሕነግ ወራሪ ኃይል በአማራ ክልል እያደረሰ ያለውን ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት አስመልክቶ ለአምባሳደሯ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በሽብር ቡድኑ የተፈናቀሉ ወገኖችን አስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ ማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይም መምከራቸውን አሚኮ ዘግቧል።
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!