የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ሹመት ሰጡ

           አቶ አገኘሁ ተሻገር

ሚያዝያ 23/2013 (ዋልታ) – የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥተዋል፡፡

በዚህም መሰረት፦

1 አቶ ሰማ ጥሩነህ በም/ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የሰላምና የህዝብ ደህንነት ቢሮሃላፊና የመልካም አስተዳደር ክላስተር አስተባባሪ

2 ፡ ኮሚሽነር ተኮላ አይፎክሩ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር

3 ፡ ኮሎነል ባምላኩ አባይ በቢሮ ሃላፊ ደረጃ የአማራ ክልል ሚሊሻ ፅ/ ቤት ሃላፊ

4 ፡ አቶ ዝጋለ ገበየሁ ምክትል ጠቅላይ ዐቃቢ ህግ

5 ፡ አቶ ሀብታሙ ሞገስ የአማራ ክልል ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር

6 አቶ ሙሉጌታ አበራ የአማራ ክልል የፍትህ ማሰልጠኛና የህግ ምርምር ኢኒስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸውን ከክልሉ ኮምንኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡