በክፍለ ከተማው ለ600 አርሶ አደሮች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ተሰጠ

                ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

ሚያዝያ 23/2013 (ዋልታ) – በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ለሚገኙ 600 አርሶ አደሮች የመሬት ባለቤትነት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ተሰጠ፡፡

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ለአርሶ አደሮች የመሬት ባለቤትነት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ አስረክበዋል።

አርሶ አደሩ በራሱ መሬት እና እርሻ ላይ ሰርቶ የመለወጥ መብቱ ሊረጋገጥለት እና ሊከበርለት ይገባል ያሉት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በደላሎችም ሆነ በህገወጥ መሀንዲሶች የሚደረግ ዘረፋ ሊቆም ይገባል ብለዋል።

የባለቤትነት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የተሰጣቸው አርሶአደሮች ተገቢውን ልማት በማካሄድ ከራሳቸው አልፈው ለከተማዋ ልማት ሊሰሩ እንደሚገባ ምክትል ከንቲባዋ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

በቀጣይም በሌሎች ክፍለ ከተሞች ለሚገኙ አርሶአደሮች የባለቤትነት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የመስጠት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከአዲስ አበባ ፕሬስ  ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።