በሐረሪ ክልል የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ እየመከሩ ነው

በሐረሪ ክልል የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች በአገራዊ እና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት እያካሄዱ ነው።

በሐረር ከተማ  በሚካሄደው ውይይት ላይ ተወላጆቹ የአካባቢያቸውን ሰላም በማስጠበቅ ረገድ ከክልሉ መንግስት ጋር በትብብር በሚሰሩበት ሁኔታ ላይ ይመክራሉ ተብሏል።

ከጁንታው ሕወሓት ቡድን ራሳቸውን በመጠበቅ ለጥፋት የተሰማሩ አካላትን አጋልጠው በሚሰጡበት ሁኔታ ላይም ይወያያሉ።

በመድረኩ ላይ የተለያዩ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ኢዜአ ዘግቧል።