የአቅመ ደካሞችንና ለሀገር ባለውለታዎች መደገፍ ሁሉም ሊሳተፉበት ይገባል – ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ


ሰኔ 20/2013 (ዋልታ) –
የከተማ አስተዳደሩ ባለሀብቶችን እና በጎፍቃደኛ ግለሰቦችን በማስተባበር የአቅመ ደካሞችን እና ለሀገር የሰሩ የሀገር ባለውለታዎች እና አስታዋሽ ያጡ አረጋዊያንን መደገፍ ሁሉም ባለሀብቶች እና በጎ ፍቃደኞች ሊሳተፉበት ይገባል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የእናት አርበኛ ወ/ሮ ማሚቴ ምህረቱ ቤት በማሳደስ አስረክበዋል፡፡
ቤቱን በፍጥነት አድሰው ላስረከቡት አቶ ሙኒር ሀይረዲን እንዲሁም የቤት ቁሳቁስ ድጋፍ ላደረጉት አቶ አለማየሁ ንጉሴ በከተማ አስተዳደሩ ስም ምክትል ከንቲባዋ አመስግነዋል።
በዘንድሮው የክረምት ወራትም በከተማዋ ከ2 ሺህ በላይ የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ ስራ መጀመሩን ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።
የከተማ አስተዳደሩ የሀገር ባለውለታዎችን አስታውሶ ቤታቸውን ከማደስ አልፎ ለተደረገላቸው የቤት ቁሳቁስ ድጋፍ መደሰታቸውን የገለፁት እናት አርበኛ ወ/ሮ ማሚቴ ምህረቱ ለተደረገላቸው ድጋፍ ማመስገናቸውን ከአስተዳደሩ ከንቲባ ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሰክሪታሪያት የተገኘነው መረጃ አመላክቷል።