የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 13 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ

የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 13 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ።
የቢሮው ኃላፊ ሙሉጌታ ተፈራ እንዳስታወቁት በ2014 በጀት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት 11 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 13 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ወይም የእቅዱን 118 በመቶ መሰብሰብ ተችሏል።
ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ወይም የ37 በመቶ ብልጫ እንዳለው ኃላፊው ተናግረዋል።
ይህንን ውጤት ማስመዝገብ የተቻለው በቢሮው ከአሰራር ጋር የተያያዙ ችግሮችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በተለይም የደረጃ “ሐ” ግብር ከፋዮች ያለ እንግልት ባሉበት ሆነው መስተናገድ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ በመዋሉ ነው ብለዋል።
የከተማው ፕረስ ሴክሬታሪያት ጽሕፈት ቤት መረጃ እንደሚያመለክተው የደረጃ “ሀ” ግብር ከፋዮች የሚጠበቅባቸውን ግብር በወቅቱ እንዲከፍሉና ከዚህ በፊት ያልከፈሉ የደረጃ “ለ” እና “ሐ” ግብር ከፋዮችም ጊዜው እየጨመረ በሄደ ቁጥር ቅጣትና ወለዱ በዛው ልክ እየጨመረ ስለሚሄድ ከወዲሁ እንዲከፍሉ ጥሪ ቀርቧል።