የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ12 ምሁራን የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ12 ምሁራን የፕሮፌሰርነት ማዕረግ መስጠቱን አስታወቀ።

ዩኒቨርስቲው የፕሮፌሰርነት ማዕረግ የሚሰጣቸው ምሁራን በመማር ማስተማሩ፣ በጥናትና ምርምር፣ በዩኒቨርስቲ ውስጥ አገልግሎት እንዲሁም በማህበረሰብ አቀፍና ሙያዊ አገልግሎት እና ለዓለም የዕውቀት ስርጸት መዳበር ስኬታማ አበርክቶ ላደረጉ መምህራን እና ተመራማሪዎች  መሆኑ ተገልጿል፡፡

በዚህም የኒቨርስቲው በሚመለከታቸው የትምህርት ክፍሎች ተመርምሮ፣ በየኮሌጆች አካዳሚክ ጉባዔዎች ተፈትሾ፣ በዩኒቨርስቲው ሴኔት ታይቶ እና ይሁንታ አግኝቶ የቀረበለትን መረጃ የተመለከተው የዩኒቨርስቲው የሥራ አመራር ቦርድ ለ12 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አፅድቋል።

የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የተሰጣቸው  ዶክተር ይልማ ስለሺ፣  ዶክተር አለሙ መኮንን፣  ዶክተር አለማየሁ ገዳ፣ ዶክተር በርሲሳ ኩምሳ፣ ዶክተር ገበየሁ ጎሹ፣  ዶክተር ሙሉጌታ አጥናፉ፣ ዶክተር ጌታቸው ተረፈ፣  ዶክተር አሰፋ ፍስሃ፣  ዶክተር  ንጋቱ ከበደ፣  ዶክተር  ግርማ ዘርአዮሐንስ፣ ዶክተር ሽመልስ አድማሱ እና ዶክተር አታላይ አየለ መሆናቸውን ከዩኒቨርስቲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛው የፌስቡክ ገፃችን

https://www.facebook.com/waltainfo
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛው የትዊተር ገፃችን
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!