የአዲስ ወግ ውይይት ሐሰተኛ መረጃ በሰላማዊ ምርጫ ላይ የሚያስከትለውን አሉታዊ ተጽዕኖ መግታት በሚቻልበት አግባብ ላይ እየመከረ ነው

የአዲስ ወግ ውይይት ሐሰተኛ መረጃ በሰላማዊ ምርጫ ላይ

መጋቢት 22/2013 (ዋልታ) – የአዲስ ወግ ውይይት ሐሰተኛ መረጃ በሰላማዊ ምርጫ ላይ የሚያስከትለውን አሉታዊ ተጽዕኖ መግታት በሚቻልበት አግባብ ላይ እየመከረ ነው፡፡

“ሰላም እና ደህንነት በምርጫ ወቅት” ለሩብ ዓመት በሦስት ክፍል ሲካሄድ የቆየው የአዲስ ወግ ውይይት ዛሬ ይቋጫል፡፡

የዛሬው ውይይት ሐሰተኛ መረጃ በሰላማዊ ምርጫ ላይ የሚያስከትለውን አሉታዊ ተጽዕኖ መግታት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ አተኩሮ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት እየተካሄደ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የቮይስ ኦፍ አሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ አገልግሎት አስተባባሪ እስክንድር ፍሬው በአወያይነት፣ የዓለም አቀፍ ተቋም የመረጃ ማጣሪያ ባለሙያ ኤደን ብርሀኔ እና መገናኛ ብዙሀን ተኮር የሕግ ባለሙያ ሰለሞን ጎሹ በተወያይነት መሳተፋቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።