326 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ አረብያ ተመለሱ

ሰኔ 07/2013 (ዋልታ) – 326 ኢትዮጵያዊያን ከሳኡዲ አረብያ ሪያድ ከተማ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ለተመላሾቹ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ተወካይ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው አቀባበል ማድረጋቸውን ከሚኒስቴሩ ቃልአቀባይ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡