የአፍሪካ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ፖሊሲ ምክክር እየተካሄደ ነው

መስከረም 13/2014 (ዋልታ) በአፍሪካ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ፖሊሲ ላይ ትኩረት ያደረገ ወርክሾፕ በቂሊንጦ ኢንዱስትሪያል ፓርክ በመካሄድ ላይ ነው፡፡

ወርክሾፑ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ በጀርመን ጂአይዜድ እና በአፍሪካ ህብረት ትብብር የተዘጋጀ ነው፡፡

በወርክሾፑ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የተለያዩ ጥናቶች ለተሳታፊዎች ቀርበው በአፍሪካ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ዙሪያ ሰፊ ውይይት እንደሚደረግ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!