የፓን አፍሪካን ወጣቶች ጉባኤ ተካሄደ

ግንቦት 17/2014 (ዋልታ) አፍሪካዊያን ወጣቶች ያላቸውን እምቅ አቅም ወደ አንድ በማምጣት ለአኅጉራቸው የተሻለ ሥራ እንዲሰሩ በማለም የተዘጋጀ የመጀመሪያው የፓን አፍሪካን ወጣቶች ጉባኤ በአዲስ አበባ ተካሄደ።

አፍሪካዊያን ካለፉት ነገሮች እየተማሩ የወደፊት ራዕያቸውን ጥሩ ለማድረግ መስራት እንደሚገባቸው በመድረኩ ተነስቷል።

አፍሪካዊያን አንድነታቸውን ይበልጥ በማጠናከር ለዓለም አንድ መሆናቸውን የሚያሳዩበት ነውም ተብሏል።
በመድረኩ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) እና የአፍሪካ ወጣቶች እድገት ማዕከል ዳይሬክተር ፉዓድ ገና ተገኝተዋል።
በሱራፌል መንግሥቴ