የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን፣የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን እና የፌደራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በጋራ ችግኝ ተከሉ

ሐምሌ 2፣ 2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን፣ የኢፌድሪ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን እና የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት በጋራ በሆለታ ከተማ ችግኝ ተክለዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ከ300 በላይ የሚሆኑ የሶስቱ ተቋማት ሰራተኞች የተሳተፉ ሲሆን ÷ በዚህም 2 ሺህ የሚጠጉ ችግኞች መተከላቸው ነው የተገለጸው፡፡

ሰራተኞቹ መሰል የችግኝ ተከላ ፕሮገራሞች ኢትዮጵያ ለምትገነባቸው ታላላቅ የሃይል ፐሮጀክቶች እና ልማቶች ተፈጥሯዊ ሚዛን በመስጠትና ዘላቂነታቸውን በማረጋገጥ ረገድ የማይተካ ሚና እንደሚኖራቸው ገልፀዋል፡፡

የችግኝ ተከላ በመርሃ ግብሩ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውሃ በሚሞላበት በዚህ ወቅት መካሄዱ የሃገሪቱን የዝናብ ወይም የውሃ መጠን ለማሳደግ የሚረዳ ተግባር እንደመሆኑ ትልቅ ኩራት እንደሚሰማቸው መናገራቸውን ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡