የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን

መጋቢት 23/2013 (ዋልታ) – በ33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማለፋን ያረጋገጠው የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት።

በአቀባበል ስነስርዓቱ ላይ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሰው፣ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤሊያስ ሽኩር፣ ም/ኮሚሽነር አቶ ዱቤ ጅሎ እና ሌሎች የስፖርት ቤተሰቦች ተገኝተው ቡድኑን አበረታተዋል።

ብሔራዊ ቡድኑ ዛሬ ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ ከአረፈበት ሆቴል ተነስቶ በአዲስ አበባ በተመረጡ ዋና ዋና ጎዳናዎች ለህዝቡ ደስታቸውን ይገልፃሉ፤ ህዝቡም ለብሔራዊ ቡድኑ ያለውን ድጋፍ እና አክብሮት የሚገልፅ ይሆናል መባሉን ከኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።