በሁሉም ቦታ በደረሰው ጥቃት አጸፋ እርምጃ በክልልና በፌዴራል መንግስት ቅንጅት እየተወሰደ ይገኛል- ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

መጋቢት 23/2013 (ዋልታ) – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በሁሉም ቦታ በደረሰው ጥቃት አጸፋ እርምጃ በክልልና በፌዴራል መንግስት ቅንጅት እየተወሰደ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “በኦሮሚያ ክልል በምእራብ ወለጋ ዞን በንጹሐን ዜጎች ላይ የደረሰውን ጥቃት እናወግዛለን፤ የተሰማንን ጥልቅ ኀዘን ለሟች ቤተሰቦችና ለኢትዮጵያውያን ሁሉ እንገልጻለን” ብለዋል፡፡