የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከተወሰደው ገንዘብ 95 በመቶ ማስመለሱን ገለጸ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ሚያዝያ 9/2016 (አዲስ ዋልታ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም ከተከሰተው የሲስተም ችግር ጋር በተገናኘ ያለአግባብ ተወስዶ ከነበረው ገንዘብ 95 በመቶ የሚሆነውን ማስመለሱን አስታወቀ።

ባንኩ ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ በተጠቀሰው ዕለት በተፈጠረ ችግር ምክንያት ብር 801 ሚሊዮን 417 ሺሕ 747.81 ያለአግባብ ተወስዶ እንደ ነበር መገለጹ ይታወሳል።

ከተወሰደው ገንዘብ 762 ሚሊዮን 941 ሺሕ 341 ብር ማስመለስ መቻሉን ባንኩ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ባወጣው መረጃ አመልክቷል።

ይህም መሰብሰብ ከነበረበት ገንዘብ ውስጥ 95 በመቶ የሚሸፍን ሲሆን ቀሪውን 38 ሚሊዮን 474 ሺሕ 938 ብር የማስመለስ ስራ እንደሚቀጥልም ገልጿል።