የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አንጎላ ዕለታዊ በረራ ሊጀምር ነው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ

የካቲት 7/2016 (አዲስ ዋልታ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አንጎላ ዋና ከተማ ሉዋንዳ ዕለታዊ በረራ ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ።

አየር መንገዱ በአሁኑ ወቅት በሳምንት አምስት ጊዜ እየበረረ ሲሆን ከመጋቢት 22/2016 ዓ.ም ጀምሮ በየቀኑ ወደ ሉዋንዳ መብረር እንደሚጀምር ነው የገለፀው።

ላለፉት 38 ዓመታት ወደ ሉዋንዳ በረራ ሲያደርግ መቆየቱን የገለጸው አየር መንገዱ ወደ ከተማዋ የሚደረገው በረራ ዕለታዊ መሆን እያደገ የመጣውን የአንጎላ ምጣኔ ሐብታዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ እንዲጎለብት ያግዛል ተብሏል።

በተጨማሪም አየር መንገዱ ከሚበርባቸው ከ135 በላይ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ጋር በየዕለቱ ለማስተሳሰር የጎላ አስተዋፅዖ እንደሚኖረው ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።