የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ይገኛል

ሚያዝያ 8/2015 (ዋልታ) የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ይገኛል።

የሃይማኖት አባቶቹ የትንሣኤ በዓልን በማስመልከት ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ለሰው ልጅ ደህንነትና ሰላም የተገኘበት መሆኑን አመልክተዋል።

በዓሉ ሲከበር በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ የተገኘውን ዕርቅ እና ሰላም ተምሳሌት በማድረግ ምዕመናን ለሀገር ሰላምና፣ አንድነት መረጋገጥ ተግቶ ሊሰራ ይገባልም ሲሉም አሳስበዋል።

በኢትዮጵያ በአንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋሉ የሰላም መደፍረስ ችግሮችን በውይይት እና በመግባባት ሊፈቱ እንደሚገባም አውስተዋል።

በዓሉን ከችግረኛ ወገኖች ጋር በአብሮነት ማሳለፍ እንደሚገባም የሃይማኖት አባቶቹ በመልዕክታቸው አስገንዝበዋል።